አሜሪካ በ2030 ወደ ሶስተኛ የዓለም ኢኮኖሚ ደረጃ ዝቅ ልትል ትችላለች

0

አሜሪካ እ.አ.አ በ2030 ከቻይና እና ህንድ በመቀጠል ወደ ሶስተኛ የዓለም ኢኮኖሚ ደረጃ ዝቅ ልትል እንደምትችል የእንግሊዙ ፋይናንሽያል አገልግሎት ተቋም ስታንዳርድ ቻርተርድ ግምቱን አስቀመጠ፡፡

በዚህም ቻይና የዓለምን የኢኮኖሚ ደረጃ ከአሜሪካ እንደምትወስድ ነው ድርጅቱ ባወጣው የዓመቱ አስር ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ አገራት የኢኮኖሚ ደረጃ ሪፖርቱ ያስታወቀው፡፡

የድርጅቱ ሪፖርት ወቅታዊው ዓለም አቀፍ የገበያ ድርሻን በመመልከት በ2030 ቻይና የአንደኝነቱን ስፍራ ልትይዝ ትችላለች ሲል ጠቁሟል፡፡

የዓለምን የኢኮኖሚ ደረጃ ኢንዶኔዥያ አራተኛ ደረጃ እንደምትይዝ ነው የተገመተው፡፡

ደረጃው የሚሰጠው የዓለምን ጠቅላላ ኢኮኖሚና ከአገራት የህዝብ ቁጥር ብሎም የሚያመነጩትን ኢኮኖሚ መሰረት በማድረግ ነው፡፡

ምንጭ፡- ዴይሊ ሜይል

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.