በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ዐረብ ሀገራት የሚሄዱ ስደተኞች ኤርትራን እንደመውጫ ይጠቀማሉ

0

ሪፖርተር የቦሌ አየር ማረፊያ ኬላዎች ማስተባበሪያ ክፍልን ጠቅሶ እንደዘገበው በጎብኝ ስም ለመውጣት የሚፈልጉ ስደተኞቹ አየር ማረፊያው ላይ ማሕበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ያወጣቸውን አዲስ ጥብቅ መስፈርቶች ስለማያሟሉ በሕገ ወጥ መንገድ በኤርትራ በኩል መውጣት ጀምረዋል፡፡ ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ በተለይ ኤርትራዊያን ስደተኞች ከፍተኛ ገንዘብ ስለሚከፍሉ ደላሎችም ፊታቸውን ወደ ኤርትራ አዙረዋል ብሏል፡፡

26 ኤርትራዊያን በቱርሚና ኦሞራቴ በኩል በመኪና ወደ ኬንያ ሲወጡ ከቀናት በፊት ተይዘዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፓስፖርት አውጥተው ወደ ውጭ ሊወጡ ሲሉ የተያዙም አሉ፡፡ ኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ላይ 5 ኬላዎችን ለማቋቋም ስምምነት የተደረሰ ቢሆንም እስካሁን ተፈጻሚ አልሆነም፡፡

ሕገ ወጡ ፍልሰት የተባባሰው ጦር ሠራዊቱ ከድንበር ላይ ከተነሳ ወዲህ ነው፤ እናም ለችግሩ መፍትሄ ለማበጀት እየሰራሁ ነው ብሏል ሚንስቴሩ፡፡

Via Ethiopia Reporter

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.