የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሀላፊዎች የሚድያ ገለፃ

0

በኤልያስ መሰረት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሀላፊዎች በትናንትናው እለት በርከት ላሉ የሚድያ አካላት ገለፃ ካደረጉ በሁዋላ በአየር መንገዱ ዙርያ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል። ከተነሱት ነጥቦች ዋና ዋናዎቹ:

– አየር መንገዱ ቪዥን 2025 የተባለውን እቅዱን ቀድሞ ስላሳካ ሌላ የ2030 እቅድ ነድፏል።
– በመስሪያ ቤቱ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን እናውቃለን። ሰራተኞች የመስሪያ ቤቱን ችግር መፍቻ ክፍሎች በመከተል ጉዳያቸውን መከታተል ይችላሉ። በዚህም ካልተፈታ በመደበኛ የፍርድ ቤት ሂደት መስመርንም መከተል ያስፈልጋል።
– የአየር መንገዱ የብድር መጠን አሁን ላይ ወደ 2.4 ቢልዮን ዶላር ገደማ ነው። ይህም ድርጅቱ አሁን ካለው ሀብት አንፃር ሲታይ በአለም አቀፍ ደረጃ ትንሽ የሚባል ነው።
– ተወልደ አውሮፕላን አለው እየተባለ በሶሻል ሚድያ የሚወራው ሀሰትም አስቂኝ ነው። የተባለው አውሮፕላን አየር መንገዱ በሊዝ ተከራይቶ እየተጠቀመበት ያለ ነው።
– አንድ ወይም ሁለት ድሪምላይነር አውሮፕላኖቻችን በ Rolls Royce የተሰሩት ኢንጅኖቻቸው ችግር ስለገጠማቸው ቆመዋል። ለዚህ ግን ሊዝ ያረገልን ድርጅት በቀን 100,000 ዶላር እየከፈለን ነው።
– ከሀጅ ጋር በተያያዘ ስለተነሳው ጉዳይ: ችግሩ የእኛ ሳይሆን ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊወስዳቸው ተስማምቶ በሁዋላ መንገደኞቹን ትቶ የሄደው የሳውዲ አየር መንገድ ነው። እኛ ከዛ በሁዋላ የበረራ ፈቃድ ጠብቀን እና አውሮፕላን አዘጋጅተን ወስደናቸዋል።
– ከቀናት በሁዋላ ዲሴምበር አንድ ኢትዮጵያ- ሞዛምቢክ የተሰኘ አየር መንገድ ሞዛምቢክ ውስጥ ስራ ይጀምራል። ሙሉ ባለቤቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይሆናል።
– አዲሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆቴል በቅርቡ ስራ የሚጀምር ሲሆን ሁለተኛው ዙር ግምባታም ተጀምሯል። ሁለቱም በአጠቃላይ ከ1,000 በላይ ክፍሎች ይኖራቸዋል።

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.