ጃይር ቦልሶነሮ የብራዚል ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን አሸነፉ

0

የቀኝ ዘመሙ እጩ ጃይር ቦልሶነሮ የብራዚል ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ተነግሯል።

ጃይር ቦልሶነሮ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን 52 ነጥብ 2 በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፉ ሲሆን፥ ተፎካካሪያቸው የነበሩት የግራ ዘመሙ እጩ ፈርናንዶ ሀዳድ 44 ነጥብ 8 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸው ተነግሯል።

ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ያሸነፉት ጃይር ቦልሶነሮ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት በሀገሪቱ ያለውን ሙስና ለመቀነስ እና በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ወንጀል ለመከላከል እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸው ተነግሯል።

ጃይር ቦሊሶነሮ ፕሬዚዳንታዊ መርጫውን ማሸነፋቸውም በላቲን አሜሪካዋ ሀገር ዴሞክራሲ አዲስ ነገር ነው ተበላለ።

ላለፉት 13 ዓመታት በግራ ዘመሙ የሰራተኞች ፓርቲ ስትመራ የነበረችው ብራዚልም አሁን በቀኝ ዘመም ፓርቲ እንድትመራ የደረገ ነው ተብሏል።

ብራዚል የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዲልማ ሮሴፍ ከስልጣን አንዲነሱ መደረጉን ተከትሎ ላለፉት ሁለት ዓመታት በፕሬዚዳንት ሚሼል ቲመር ስትመራ ቆይታለች።

ምንጭ፦ www.bbc.com

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.