ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከቮልስ ዋገን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

0

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጀርመኑ መኪና አምራች ቮልስ ዋገን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ። የቮልስ ዋገን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ኩባንያቸው በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ጽኑ ፍላጎት እንዳለው በዚህ ወቅት ገልጸዋል። ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቹ ኩባንያቸው በኢትዮጵያ ፋብሪካ ማቋቋም የሚያስችለውን ጥናት እያደረገ መሆኑንም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ለኩባንያው ፍላጎት መሳካት መንግስት ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። አያይዘውም ኩባንያው በተቻለ ፍጥነት ጥናቱን አጠናቆ ውሳኔውን እንዲያሳውቅ መናገራቸውን፥ በስብሰባው ላይ የተገኙት የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።

ቮልስ ዋገን መቀመጫውን በወልፍስበርግ ያደረገ የጀርመን ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ነው።

ኩባንያው በተለይም ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎችን በማምረት በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ገናና ስም ገንብቷል።

አለም ላይም ባለው ገቢም ከቀዳሚዎቹ 10 ኩባንያዎች ተርታ መሰለፉ ይነገራል።

ከፈረንጆቹ 19 37 ጀምሮም በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.