ዶ/ር አብይ ፕሬዚዳንት የመክፈቻ ንግግር ዙሪያ ዛሬ በምክር ቤቱ ቀርበው የመንግስታቸውን አቋም ያብራራሉ

0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለህዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስብሰባ ባቀረቡት ንግግር ላይ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የመንግስታቸውን አቋም ያብራራሉ።

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ባለፈው ሳምንት በምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ ላይ የመንግስትን 2011  የትኩረት አቅጣጫዎች ያመላከተ ንግግር ማቅረባቸው ይታወሳል።

ምክር ቤቱም በዛሬው እለት የፕሬዚዳንቱን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ምርጫም እንደሚከናወን የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

ምክር ቤቱን ለላፉት ወራት በአፈጉባኤነት ሲያገለግሉ የነበሩት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በዚህ ሳምንት ያቀረቡትን መልቀቂያ ምክር ቤቱ መቀበሉን ተከትሎ፥ ወይዘሮ ሙፈሪያት አዲስ ለተቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መሾማቸው ይታወቃል።

Via FBC

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.