የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዛሬው እለት የጋራ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ያካሂዳሉ

0

የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዛሬው እለት የጋራ የመክፈቻ ስነ ስርዓት እንደሚከፍቱ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል ተናገሩ። የጋራ ምክር ቤቶቹ 5ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ አንደኛ መደበኛ ጉባዔን እንደሚያካሂዱም ተናግረዋል።

አፈ ጉባኤዋ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ምክር ቤቱ ባለፉት 4 ወራት የማሻሻያ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል። ከዚህ ውስጥ ምክር ቤቶቹን ከህብረተሰቡ ጋር የሚያገናኙና ተሳትፎን የሚያሳድጉ እንደ ነጻ ጥሪ ማዕከል መተግበሪያ መሰራታቸውንም ነው የተናገሩት። ከዚህ ባለፈም የምክር ቤቱን ተደራሽነት ለማስፋት የራሱን ሚዲያ ለማቋቋም በሂደት ላይ መሆኑንና በተጠሪ ተቋማት ላይ የሚደረግ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች ስራዎች መሰራታቸውንም ገልጸዋል።

አብዛኛዎቹ የማሻሻያ ስራዎች የተጠናቀቁ ሲሆን ቀሪ ስራዎች ደግሞ እስከ ጥቅምት አጋማሽ ተጠናቀው ወደ ስራ ይገባሉም ነው ያሉት።

በተያዘው በጀት አመትም ምክር ቤቶቹ የህዝቡን ፍላጎት የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት፥ ያልተቋረጠ ብቃት ያለው የአቅም ግንባታ ለአመራሮችና አባላት ለመስጠት አቅጣጫ መያዙንም አፈ ጉባኤዋ ጠቅሰዋል።

Via FBC

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.