ጨፌ ኦሮሚያ በክልል ደረጃ የነበሩ የቢሮ ቁጥሮችን ከ42 ወደ 38 ዝቅ እንዲሉ ወሰነ

0

ጨፌ ኦሮሚያ የክልሉን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማደራጀትና ስልጣንና ሃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣው አዋጅ አፀደቀ።

የጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባዔው በጥዋት ውሎውም የክልሉን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማደራጀትና ስልጣንና ሃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

ረቂቅ አዋጁ ችግር የሚስተዋልበትን የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት፣ የሰው ሃይልና በጀት አጠቃቀም ላይ የሚስተዋለውን ሰፊ ክፍተት የሚቀርፍ መሆኑ በጉባዔው ላይ ተነስቷል።

ከዚህ ባለፈም በቢሮ ደረጃ ተከማችተው የሚገኙ የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀቶች ታች ካለው ማህበረሰብ ጋር ቀርበው እንዲያገለግሉ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ሚና ይኖረዋልም ነው የተባለው።

ከዚህ በፊት በነበረው አደረጃጀት በክልል ደረጃ 42 የነበሩ ቢሮዎች በዛሬው እለት በፀደቀው አዋጅ መሰረት ወደ 38 ዝቅ እንዲደረጉም ተወስኗል።

በአዲሱ አደረጃጀት መሰረትም፦

1. የርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት

2. የእርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ

3. የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ

4. የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

5. የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

6. የትምህርት ቢሮ

7. የጤና ጥበቃ ቢሮ

8. የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ

9. የውሃ እና ኢነርጂ ልማት ቢሮ

10. የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ

11. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

12. የንግድ ቢሮ

13. የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ

14. የባህልና ቱሪዝም ቢሮ

15. የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

16. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ

17. የኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ

18. የትራንስፖረት ባለስልጣን

19. የመንገዶች ባለስልጣን

20. የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን

21. የአካባቢ፣ የደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን

22. የኮንስትራክሽን ባለስልጣን

23. የማእድን ልማት ባለስልጣን

24. የግብርና ግብአቶች ቁጥጥር ባለስልጣን

25. የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና መገናኛ ባለስልጣን

26. የአርብቶ አደር አካባቢዎች ልማት አስተባባሪ ኮሚሽን

27. የእቅድና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን

28. የኢንቨስትመንት ኮሚሽን

29. ፖሊስ ኮሚሽን

30. የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን

31. የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

32. ስፖርት ኮሚሽን

33. የህብረት ስራዎች ማስፋፊያ ኤጀንሲ

34. የእንስሳት ሀብት ልማት ኮሚሽን

35. የገበያ ልማት ኮሚሽን

36. የግብርና ጥናት ኢንስቲቲዩት

37. የከተሞች ፕላን ኢኒስቲቲዩት

38. የመንግስት ህንፃዎች አስተዳደር በመሆን በአዲስ መልክ ተደራጅተዋል።

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.