ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክን ዛሬ መርቀው ከፈቱ

0

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክን ዛሬ መርቀው ከፈቱ። የኢንዱስትሪ ፓርኩን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳና እና ሌሎች የክልል ርእሳነ መስተዳድራን፣ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት እንዲሁም የአካባቢ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ግንባታው በ2009 ዓመተ ምህረት ጥቅምት ወር ላይ የተጀመረው ይህ ፓርክ፤ በ102 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ከ147 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ነው ግንባታው የተካሄደው፡፡ ፓርኩ በተለያየ ዘርፍ ለሚሰማሩ ኩባንያዎች የሚያገለግሉ 19 የመስሪያ ሼዶች ወይም የመስሪያ ቦታዎችን የያዘ ነው።

ከእነዚሀ ሼዶች ውስጥም ስድስቱ 11 ሺህ ካሬ ሜትር፣ ዘጠኙ 5 ሺህ 500 ካሬ ሜትር፣ አራቱ ደግሞ በ3 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፉ ናቸው። ፓርኩ በተሟላ ሁኔታ የማምረት ደርጃ ላይ ሲደርስ ከ1 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ሀገሪቱ ከወጪ ንግድ እንድታገኝ የሚያስል ሲሆን፥ ከ60ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ደግሞ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል። ጃንሱ-ሰንሻይን እና ኪንግደም የተባሉ ሁለት ግዙፍ የግል ፉብሪካዎችም በፓርኩ ውስጥ በግንባታ ላይ ናቸው። ጃንሱ-ሰን ሻይን በ80 ሄክታር እንዲሁም ኪንግደም በ30 ሄክታር ላይ የሚያርፉ የጨርቃ-ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካዎች ናቸው።

Via FBC

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.