ጀርመን የ2024ን የአውሮፓ ዋንጫ ለማዘጋጀት ተመረጠች

0

በስዊዘርልንድ ኒዮን በተዘጋጀው የመጨረሻው መድረክ ላይ ጀርመን ቱርክን በመርታት የ2024ን የአውሮፓ ዋንጫ ለማዘጋጀት ተመረጠች፡፡

ጀርመን ይህ በ2024 የምታስተናግደው የአውሮፓ ዋንጫ የምዕራቡና የምስራቁን ግንብ አፍርሳ አንድ ሀገር ከሆነች በኋላ የምታስተናግደው የመጀመሪያው ውድድር ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም የአውሮፓ ዋንጫን ለማዘጋጀት በ2008፣ በ2012 እና በ2016 ፉክክር ውስጥ ገብታ ሳይሳካላት መቅረቱ የሚታወስ ነው፡፡

በ2024 የአውሮፓ ዋንጫ 24 ሀገራት እንደሚሳተፉ የተጠቀሰ ሲሆን በጥቅሉ ለ32 ቀናት ውድድሩ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

የቀድሞ የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋችና አምበል ፊሊፕ ላኻም ለሃገሩ አምባሳደር በመሆን ቅስቀሳ ሲያደርግ የነበረ ሲሆን ከጀርመን መመረጥ በኋላ እግርኳስ የሚወዱ ደጋፊዎች ውድድር ለማዘጋጀት የተሰናዱ ስታዲየሞች እንዳሏቸውም ጠቅሷል፡፡

ከዚህ ቀደም ብሎ የሚዘጋጀው የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ በ12 የአውሮፓ ከተሞች ይሰናዳል ተብሏል፡፡

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.