ሌበር ፓርቲ ብሪታንያ በህብረቱ አባልነት እንድትቆይ ዳግም ሪፈረንደም መካሄድ እንዳለበት አስታወቀ

0

የብሪታንያው ዋነኛው የፖለቲካ ፓርቲ የሆነው ሌበር ሀገሪቱ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የምታደርገውን ፍቺ ላለመቀበል በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ተሰማ፡፡

ሌበር በተጨማሪም በጉዳዩ ላይ ብሪታንያ ዳግም ሪፈረንደም የምታካሄድበትን አማራጭ እያሰበ ነው ተብሏል፡፡

የሌበር ፓርቲ ሊቀመንበር ጀርሚይ ኮርበን ሀገራቸው በአውሮፓ አባልነት ቆይታዋ ላይ ዳግም ጠቅላላ ምርጫ እንድታካሂድ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡

የዳግም ሪፈረንደም ጉዳዩ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁለት ፓርቲዎችን በተራራቀ አቋም ላይ እንዲገኙ አድርጓቸዋል ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ በሚያቀርቡት የ’ብሪግዚት’ የፍቺ አማራጭ ሐሳብም እንደማይቀበሉ የሌበር ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም ሜይ የሚያቀርቡትን ሐሳብ ባለመቀበል ብሪታንያ በህብረቱ እንድትቆይ የሚያስችላትን ሪፈረንደም እንድታካሄድ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

ሌበር ፓርቲ የብሪታንያን ኢኮኖሚን ይጎዳል በማለት ነው እነዚህን ሁለት ምርጫዎች ያስቀመጠው ተብሏል፡፡

ብሪታንያ ከአውሮፓ አባልነት ለመውጣት የቀራት ጊዜ ስድስት ወራት ሲሆን ፍቺው በተፈለገው ፍጥነት እየሄደ አይደለም እየተባለ ይገኛል፡፡

ምናልባትም ብሪታንያ በዚህ አያያዟ ከቀጠለች በ2016 ያደረገችውን ሪፈረንደም ዳግም ልትከልሰው እንደምትችልም የህብረቱ አባል ሀገራትና የፖለቲካ ተንታኞች ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.