13ኛው የህወሃት ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ 1 ሺህ 650 ሰዎች በድምፅና ያለ ድምፅ እየተሳተፉበት ይገኛሉ

0

13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህወሃት/ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ መካሄድ ጀመረ።

በመቐለ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው 13ኛው የህወሃት ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ 1 ሺህ 650 ሰዎች በድምፅና ያለ ድምፅ እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

ከዚህ በተጨማሪም በጉባኤው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችም ተሳታፊዎች ናቸው።

ጉባኤው የኦዲት ሪፖርትን የሚያደምጥ ሲሆን፥ በ12ኛው ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች አፈፃፀምንም ይገመግማል።

ከዚህ በተጨማሪም በድርጅታዊ ጉባዔው ሀገራዊ ሁኔታውን ከድርጅቱ እና ከትግራይ ህዝብ አንፃር የሚመለከት መነሻ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

የድርጅቱን ህገ ደንብ ለማሻሻልል በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ተወያይቶም ውሳኔ ያሳልፋል ማሳለፍ እና የቀጣይ ዓመታት አቅጣጫዎችን ማስቀመጥም ከጉባኤው ይጠበቃል።

“የአንድነትና የፅናት ጉባኤ ለህዳሴያችን” በሚል ስያሜ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፥ ህዝባዊነታቸን ለጽናታችንና ድላችን መሰረት ነው የሚል መሪ ቃል ያለው መሆኑም ተጠቅሷል።

በዚሁ ጉባኤም የድርጅቱን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ይመርጣል።

Via EBC

Share.

About Author

Ethio Newsflash is all about news stories from Ethiopia and beyond!

Comments are closed.